Friday, June 15, 2012

Generation “?”

ትውልድ ይሄዳል የሄደውን ለመተካት ደግሞ ሌላ ትውልድ የመጣል፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ማህተም አስቀምጦ በሌላ ይተካል፡፡ በምዕራቡ አለም በተለያየ ጊዜ የሚመጡ ትውልዶች የትወልዱን ባህርያት መሰረት በማድረግ የተለያየ የጊዜ ክፍፍል እና የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደዚህ፡

[caption id="attachment_89" align="alignright" width="604"] courtesy "http://www.addisfortune.com"[/caption]

The Lost Generation ፡ ይሄ ትውልድ ከ19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እስከ አንደኛው የአለም ጦርነት መጨረሻ የነበረው ሲሆን በጦርነቱ ማብቂያ ህልውናው ያከተመ ነው፡፡

The Silent Generation፡ ይህ ዝምተኛ ትውልድ ደግሞ የአንደኛው የአለም ጦርነት ከተጠናቀቀበት እስከ ታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት (The Great Depression) ድረስ የነበረው ሲሆን በአመዛኙ ድብታ የዋጠው ነበር፡፡

The Greatest Generation: ታላቁ ትውልድ የተሰኝው ደግሞ ታላቁን የኢኮኖሚ ድቀት ተቋቁሞ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተፈትኖ ያለፈው እና እንደ ብረት የጠነከረ የተባለው ነው፡፡

Generation X፡ ይህ ትውልድ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ የ1960ዋቹን አለማቀፍ የነፃነት፣ የአንድነት እንዲሁም የፀረ-ጦርነት ሰልፎች ሲያካሂድ የነበረ እና በባህል ለውጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገው ትውልድ ነው፡

Generation Y or The Millennial Generation:  የ Generation X ተከታይ ትውልድ ሲሆን በቴሌቪዥን እና በዲጅታል ሚዲያዎች ፍቅር የወደቀ እንዲሁም በሁሉም ነገር ለዘብተኛ ሊባል የሚችለው ትውልደ ነው፡፡

Generation Z፡ የDotcom Bubble ውጤት የWorld Wide Web ፍሬ እና ቀሰስተኛው ትውልድ ሲሆን ዘመኑም አሁን ነው ይላሉ፡፡

እነዚህን እና የመሳሰሉትን የትውልድ ተረኮች አሉ፡፡

ወደ ሀገር እኛ ሁኔታ ስንመጣ  መሰረታዊ የሆነ የትውልድ ልዩነት፣ ጊዜ እንዲሁም ስያሜ አለ ማለት ባይቻልም በተለምዶ 'ያ ትውልድ' እየተባለ የሚጠራው እና የኢትየጵያን አብዮት የመራው እንዲሁም ከ ሶሻሊዝም ጋር በፍቅር ያበደው ትውልድ እንደ አንድ ትውልድ ይዘን ወደፊት እና ወደኋላ መሄድ እንችላለን፡፡

ከ ጣሊያን ወረራ እስከ ያትውልድን ድረስ ያለውን ዘመን 'የነፃነት ትውልድ' ልንለው እንችላለን ህይወቱ ሁሉ በወረራው ዘመን የተቃኝ በመሆኑ፡፡ ኑሮው ሁሉ የአርበኛ እና ባንዳ ፉክክርን ያስተናገደ እንደመሆኑ፡፡ እንግዲህ በምዕራቡ አለም Generation Yዎች የ Generation X ልጆች ናቸው ካልን በኛ ሁኔታ ደግሞ ያ ትውልድ የነፃነት ትውልድ ልጆች ናቸው ማለት እንችላለን፡፡

ችግር የሚሆነው የያ ትውልድን ጊዜ ማስቀመጥ አሁን ያለውንም ትውልድ ልዩነት ማወቁ ላይ ነው፡፡ ፖለቲካል ኢኮሚውን የውልድ አባላት እስከ አሁን እንደሚያሽከረክሩት መናገሩ የተራራ ላይ ሚስጥር ነው፡፡ እና የአሁኑ ዘመን ትውልድ መለያዎችስ ምን ይሆኑ? ነገሩ ጨዋታ እንደመሆኑ ቀጣዮቹ ምልልሶች እመልከት እስኪ፡

ሊሊ እና ጄሪ

ሊሊ፡ እኔ እምልሽ Justin ፀጉሩን ተቆረጠ የሚባለው እውነት ነው?

ጄሪ፡ No way, አያደርገውም ! ይሄ ለኛ ለአድናቂዎቸ ክብር አለመስጠት ነው፡፡ ከSelinaጋር ያለውን ግንኙነት ግልፅ አለመሆን ሲገርመኝ ብሎ ብሎ ደግሞ በምንወድለት ፀጉሩ መጣ? I swear, Online petition ካለ I will do that !

ሊሊ፡ Donation ነው አሉ የሰጠው፡፡

ጄሪ፡ ኡፍፍ የዚህን ሁሉ ድሃ ሆድ የሱ ፀጉር ይሞላ ይመስል፡፡ በእውነት Lil Wayneን የምወደው ለአድናቂዎቹ ባለው ክብር ነው! Never, Babyማ ይሄን አያደርግም፡፡

ዳኒ እና ጆኒ

ዳኒ፡ የ Balotelli አይነት የፀጉር ቁርጥ ፈልጌ እዛ እነ ሚኪ ፀጉር ቤትብሄድ ገገማ ብቻ ነው የሞላበት፡፡ አንዱም እንኳን አይችሉም፡፡

ጆኒ፡ እኔ እምለው Balotelli መልበሻ ክፍል ውስጥ የሆነ ነገር ሳያደርግ አልቀረም ስልጠና ላይ ብቻውን ነበር፡፡

ፊፊ እና ቲቲ

ፊፊ፡ የKaty Perry ፀጉር Human Hair መሆኑን ትናንት ሊዮና ነግራኝ ከምር Katyን ታዘብኳት፡፡

ቲቲ፡ እንጅ እኔም ግንባሯን Botox ተሰርታለች የመል ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ Otherwise, how on earth, her skin slimmed as lip?

ባቢ እና ጃክ

ባቢ፡ Rooney ባለፈው Surgery ካደረገ በኋላ አውሮፓ ዋንጫ ላይ ከBeckham ጋር ተቀራራቢ የፀጉር ቁርጥ መቆረጡን አየህ?

ጃክ፡ አዎ ቅድም Sky Sport ላይ አይቸዋለሁ፡፡ መጀመሪውኑ በድብቅ ሰርጀሪ የተሰራ ጊዜ ነውእሱን የታዘብኩት፡፡ እሽ ለማንም ሳይናገር አንደ ነገር ቢሆን የምንጎዳው እኛ አይደለንም?

ባቢ፡ እውነትሽን እኮ ነው ጃኮ፤ ግን ፈርጊ ያስተካክለዋል ብየ አስባለሁ፡፡ ሁልጊዜም በፈርጊ እምነት አለኝ፡፡

The Lost Generation or The EPRDF Generation?

3 comments:

 1. ሁሌም ዘላለም ሲፅፍ እኔ አነባለዉ፤ እባክህ ሁሌም አነብ ዘንድ ሁሌምፃፍ ….
  የእነ ሊሊና ጀሪ፣ የዳኒና ጆኒ፣የፊፊና ቲቲ፣የባቢና ጃክ ወግ በአብዛኛዉ በዚህ “ያቃተዉ ትዉልድ” የእለት ዉሎ መመዝገቢያ ማስታዎሻ (diary) ተመዝግቦ የድግግሞሽ ዉሎ ከሆነ ቆዬ…..አቶ ዘላለም እኔን የገረመኝ ከሀገሪቱ ኤፍም የአንበሳ ድርሻዉን የሚይዘዉና በመንግስት ሰዎች የሚተዳደረዉ ፋኖ ይሁን ፋና ኤፍኤም መሆኑ ያለየለት ጋዜጠኞች ያዉም አንዱ ፊልም ሰርቶ ብቻዉን ለአንድ ኢትዮጵያዊ ባለጊዜ በአንድ ዉጭ ሃገር ሊያሳይ መሄዱን እንደ ትልቅ ሃገራዊ ጉዳይ ሲተነትኑ የነበሩ ብርሃኔ ሙሴ ንጉሴ እና ዮናስ የሚባሉ የሚያወሩትን ወሬ ልክ እንደ ሊሊና ጀሪ እንዲሁም ለተነሳዉ ጉዳይ በሚዲያ ደረጃ ስለምንስ እንደሚያወሩ…የልቀት ደረጃቸዉስ እስከምንስ ድረስ እንደሆነ …..ትዉልዱስ ከሚዲያዎች ምን እየተማረ እንዳለ እንደ ማሳያ ሊሆን ይችላል…..እንዲም ሲሉ ይቀጥላሉ
  • ጀስቲን መንገድ ላይ ሲሄድ ጫማዉ ተፈታበት……
  • ቢዮንሴና ጀዚ ሲጣሉ የሚያደርጓቸዉ አስር ነገሮች…..ጀዚ ካልሲዉን አያጥብም…..ቢዮንሴ ምግብ አትሰራም…….ብቻ እንጃ አጋር ጋዜጠኞቹም ሚስታቸዉ ጋር ሲጣሉ ካልሲያቸዉን ማጠብ እንዳያቆሙ እንጂ


  ከምር የእኛዉ የጅማዉ ጎጃሜ ጌትነት እንዬዉ ስለዚህ Generation Z እንዲህ ነበር በግጥም የሰለቀዉ

  Please እባካችሁ
  ጥንት አባቶቻችሁ አለቱን ፈልፍለዉ ፊደል የቀረፁ
  አክሱምን ያቆሙ ሩሃን ያነፁ
  በባህል በልማድ በወግ የከበሩ
  በሃገራቸዉ ስርዓት ኮርተዉ የሚኖሩ
  ነበሩ እያላችሁ ነገር አትጀምሩ
  ሙድ አታበላሹ አቦ በእናታችሁ
  እንዴ ምን ነካችሁ
  እኛ የዛሬዎች እንደ አባቶቻችን ቅኔ የምንዘርፍ
  ጥበብ የምንነድፍ
  ጠቢብ ብቻ ሳንሆን
  የአዲሱ ዓለም ስርዓት በዉቀት ያጠመቀን
  ዘመን የሚዘፍነን ዓለም የሚዘርፈን
  እኛዉ እራሳችን ቅኔዎች እኮ ነን
  ስለዚህ እባካችሁ
  ስለዚህ እባካችሁ
  ጥንት አባቶቻችሁ መርከብ አበጅተዉ ባህር ያቋረጡ
  በዕዉቀት የበለጡ በጥበብ ያጌጡ
  እንዲህ አደረጉ እንደዚያ ሰጡ
  እት እት አትበሉን ጠዋት ማታ
  አቦ ሰላም ስጡን ኳስ እንይበታ
  እንዴ ምን ነካችሁ
  እስኪ ይታያችሁ
  እንደ አፄ ቴዎድሮስ ሽጉጥ ከመጨለጥ
  ለእንግሊዝ እግር ኳስ ምን አለ እጅ ብንሰጥ
  ምን አለበት እስኪ እዚህ ከመቀመጥ
  ቪዛ ሳናስመታ ትኬት ሳንቆርጥ
  በአየር ሳንሳፈር ባህር ሳናቋርጥ
  በዲኤስቲቪ ሾልከን ብናመልጥ
  በአዲስ ዓለም ስርዓት በዕዉቀት የተጠመቅን
  ግሎቫላይዜሽን ጠልቆ የዘለቀን
  የነቃን የበቃን የገባን እኮ ነን
  ምን አለበት ታዲያ ሃርድ ባትሰጡን
  ሃገር ልማት ታሪክ ምናምን ባትሉን
  ምንል ብትተዉን
  ምናል ብትረሱን
  በእዉነት ምን ነካችሁ
  ግሎቫላይዜሽን ምናል ቢገባችሁ
  ምን አለበት እስኪ በኢትዮጵያ በሬ አሜሪካን ቢያርሱ
  እስኪ ምን አለበት ለገሃር ተኝተዉ ለደን ላይ ቢነሱ
  እኛ እኮ ልዩ ነን ቅኔ ስደተኞች
  በመንፈስ ኮብልለን ካገር ነቅለን ወጥተን
  አንድም የማንጎድል ምትሃተኛ ቁጥሮች
  ኑረንም ሄደንም ሰማኒያ ሚሊዮኖች
  እፁብ ድንቅ ነን ዉብለን እኮ ሃበሾች
  የአዲስ ዓለም ስርዓት በዉቀት ያጠመቀን
  በስቴዲየም ታጥረን ዓለምን የናቅን
  ሁሉን ነገር ትተን ሁሉንም እረስተን
  ስለኳስ አስበን ስለኳስ አዉርተን
  ከኳስ ጋር ተኝተን ከኳስ ጋር ነቅተን
  ቀን የቸልሲ ነገር ሃሳብ የሚሆነን
  ሌት የአርሰናል ጉዳይ እንቅልፍ የሚነሳን
  የማንቸ ድል መንሳት የሚያስፈነጥዘን
  የሩኒ ወለምታ የሚጠዘጥዘን
  የአንጀሊና ትዳር የሚወዘዉዘን
  እንጨነቅበት ሃሳብ የጨነቀን
  እንቸገርበት ችግር የቸገረን
  ድፍን የሃበሻ ዘር እኛ እኮ ልዩ ነን
  ምን አበት ታዲያ አቦ ባትወግሙን
  ሃገር ልማት ታሪክ ምናምን ባትሉን……..በልክ የተሰፋች ከኪራይ ሰብሳቢ ነፃ የሆነ ልብስ ሰፊ የሰፋት ስላቅ

  ReplyDelete
 2. ነገርህ ጨዋታ ቢሆንም ቅሉ

  With all due respect, I found your article ‹‹ወጣ ወጣና እንደሙቀጫ ...›› አይነት ነገር ነው የኾነብኛ

  I was wondering you will point out the the lost generations with a more serious and real way since your title shout at loud.

  The generation which lost hope and faith in the country,
  the generation in exile,
  the generation in fear of politics,
  the generation in the hands of systematic corruptions,
  the generation with out knowledge of the countries rich history,
  the generation instate of ignorance with all the necessary knowledge of what is going on around and as you mention የቲቲና የጆኒ ትውልድ- ማንነቱ የተነጠቀ ትወልድ !

  ReplyDelete