Monday, November 26, 2012

ጆማኔክስ ካሳዬ 
ኢትዮ ምህዳር (ማክሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2005 ዓ/ም)
አዲስ መታተም የጀመረችው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ገና ከመምጣቷ በማተሚያ ቤቶች እጦት እንግልት ውስጥ ገብታለች ፡፡ሁለተኛ ህትመቷን ይዛ የመጣችው ይህች ጋዜጣ ቀጣይ ህልውናዋ አደጋ ላይ መሆኑን ገልጻ ‹‹የዲሞክራሲ ያለህ!›› በሚለው ርዕሰ አንቀጽ ውስጥ ዛሬ በዘመነ ሉላዊነት(ግሎባላይዜሽን) ኢህአዴግ መራሷ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ቁልቁል ወደ ኋላ ተጉዛ ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌዋን ማክበርና መተግበር ተስኗታል፡፡ ኢህአዴግ የመሰብሰብና በነጻ የመደራጀት መብትን መተግበር ተስኖት ብዙ ነጻ ማኅበራትን ወደ ራሱ ጉያ ጠቅልሏል፣ የኃይማኖት ተወካዮች ያለ መንግስት ቡራኬ መምረጥ ፣ ለመንግስት ሳይወግኑ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ ርዕሰ ጉዳዮች መዳሰስ እና ሃሳብን በነጻነት ለማራመድና ለመግለጽ ከማይቻልበት የአዘቅት ደረጃ ላይ ኢትዮጵያ ወድቃለች ብሏል መረር ባለው ርእሰ አንቀጹ፡፡
በመቀጠልም ‹‹ በሀገሪቱ የሚካሄዱ የንግድና ኢንዱስትሪ እንቅስቀቃሴዎች በመላ በመቆጣጠር እጅግ የጠነከሩና የከበዱ ፓርቲያዊ (የኤፈርት ድርጅቶች) እና ትልልቅ ምንግስታዊ ተቋማትን በመመስረትና በመገንባት የግሉ ዘርፍ እጅግ እንዲቀጭጭና እንዲከስም አድርጓል፡፡›› …‹‹ ዛሬ ነጻ ጋዜጦች ህልውና እንዳይኖራቸው በመንግስት ማተሚያ ቤቶች የተጠና ሳንካ መፍጠር እና ማገት የተለመደ ሆኗል…›› ሲል በሌላ ተጨማሪ አንቀጹ
ኢትዮ ምህዳር በተጨማሪ ዜናዎቹ/ጽሁፎቹ
 • የኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ ስልት
 • አንድነት ፓርቲ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሹም-ሽር አካሄደ
 • የገዢው ፓርቲ የ‹‹ነገ›› ፖለቲካ- በአናንያ ሶሪ
 • የትምህርት ቁልቁለትና… በኤፍሬም በየነ
 • ‹‹አቦይ›› ስብሃትን ሳስበው ሳስበው… በጌታቸው ወርቁ
 • ቃለመጠይቅ ከቀድሞው ታጋይ ከአቶ ብርሃኑ በርኸ ጋር
የኛ ፕሬስ (ረቡዕ ኅዳር ሲታጠን 2005 ዓ/ም) የወጣው እትሙ
የኢትዮ-ግብፅ የውሃ ፖለቲካ ውጥረት በተመለከተ
 • ‹‹ግብጽ ራሷን ለመከላከል በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት የመክፈት ሕጋዊ መብት አላት፣የህዳሴው ግድብ ተጠናቀቀ ማለት ኢትዮጵያ ጠላትነቷን አስመሰከረች ማለት ነው›› የግብጽ ኤክስፐርት
 • ‹‹የህዳሴው ግድብ በአብዛኛው ግብጻውያን አልተወደደም›› አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ሲል የተለያዩ አካላት ለህዳሴው ግድብ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ አስተያየቶችን አስነብቧል፡፡
 • በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ወጣቶች ‹‹የመለስን ራዕይ ለማሳካት ተቸግረናል›› አሉ የየኛ ፕሬሰ ዜና ሲሆን እንግዲህ እነዚህ ወጣቶች በኮብል ስቶን ሥራ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም የእስካሁኑ ይበቃችኋል አሁን ወደ ቡሎኬት ሥራ ግቡ ቢባሉም ምንም የተመቻቸ ሁኔታ በሌለበትና ኮብል ስቶን የተሻለ እያገኘንበት በመሆኑ ለመቀየር ተቸግረናል ብለዋል፡፡መንግስት ቡሎኬት ማምረት ለኢትዮጵውያን ብቻ የተተወ ነው ቢልም ቱርኮች ገበያውን በተቆጣጠሩበት ሁኔታ የብሎኬት ማምረት ስራው ን ለመስራት መገፋፋታቸው የጠ/ሚኒስትን ራእይ እንዳያሳኩ እንዳገዳቸው ተናግረዋል፡፡ (ጥያቄና መልሱ ያው ካድሬን በካድሬኛ ይመስላል፡፡)
 • ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ውዝግቡን የሚያባብስ ንግግር አደረጉ ያለው የኛ ፕሬስ  ‹‹እደግመዋለሁ ዘላለማዊ ክብር ለጠ/ሚ መለስ ዜናዊ›› ማለታቸውን ጽፏል፡፡
አጫጭር ወሬዎች የኛ ፕሬስ
 • በኢትዮጵያ ላይ ለሚቃጣ ጥቃት ከኛ ከሙስሊሞች ቀድሞ አንገቱን የሚሰጥ የለም›› የኢትዮጵያ ሙስሊሞች
 • አቦይ ስብሃት በጀርመን የተቃውሞ ሰልፍ ተወጣባቸው
 • ‹‹አስኳሉን አመራር ነው ያጣነው›› አቶ ሬድዋን ሁሴን
 • ‹‹የኢትዮጵያ እግር ኳስ ትንሳኤ የተገኘው በኢትዮጵያ ሕዝብ ብርታት ነው›› አቶ አሊሚራህ መሀመድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አባል
 • ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የህገ ወጥ ሶፍትዌር ስርጭትን አስቆማለሁ›› ማይክሮሶፍት ( እነ አረጋኸኝ ምን ይሉ ይሆን?)
የኛ ፕሬስ በርዕሰ አንቀጹ “የጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርም ካቢኔ የታለ?” ሲል  ጠ/ሚኒስትሩ ሚናቸው በማይታይበት አመራር ስካቤኔያቸው ጠይቋል፡፡ 
አዲስ አድማስ  (ቅዳሜ ኅዳር 15 ቀን 2005 ዓ/ም) 
‹‹አንድነት›› በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ነገ ውይይት ያካሂዳል ሲል አድማስ የእሁዱን የአንድነት ፓርቲ የውይይት እቅድ አስተዋውቋል፡፡የገዥው ፓርቲ አፈናና ጭቆና መባባሱና የተቃዋሚ ፓርቲዎች በውይይቱ ላይ የሚነሱ ነጥቦች መሆናቸውን እና  የፓርቲው ልሳን ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ በአገሪቱ በየትኛውም ማተሚያ ቤት እንዳትታተም መታገዷን ፓርቲው ማስታወቁንም አያይዞ ገልጸዋል፡፡
ዜጎች በኮብል ስቶን ንጣፍ በሰፊው በሚሰማሩበት እና ወደ ኢንዱስት ለመሸጋገር ጥረት እያደረገ እነዳለ በሚናገርበት በዚህ ጊዜ  ሆላንድ ካር በኪሳራ ተዘጋ የሚለውን ዜና አድማስ አስነብቧል፡፡ በሃገር ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖችን ያስተዋወቀውና ብዙ ዋጋ የከፈለው ሆላንድ ካር ከቢዝነስ ሲወጣ ቻይና እያለ ሽርኩ የነበረው ሊፋን ቦታውን  ተረክቦታል፡፡ አድማስም ሊፋን ሞተርስ እየተስፋፋ ነው ብሏል በሌላ ዜናው፡፡
“ዛሬ  ቀኑ ለእኔ እጅግ የሚያሳዝን ቀን ነው፡፡ ብዙ ራዕይ ነበረን፤ ብዙ ገንዘብም አፍስሰን ነበር ሆኖም እንዳሰብነው ሊሆንልንና ሊሳካልን ባለመቻሉ ኩባንያችን እንዲዘጋ ግድ ሆኗል”  የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ  ስለ ሆላድ ካርስ መዘጋት የተሰማቸውን ሃዘን ተናግረዋል፡፡
አጫጭር ወሬዎች/ዜናዎች አዲስ አድማስ
 • ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ድርድር እንፈልጋለን አሉ- የምርጫ ስነምግባሩን ካልፈረሙ ፓርቲዎች ጋር አንደራደርም›› ኢህአዴግ
 • 3ቱ የኑሮ ችግሮች የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች 3 የምርጫ አጀንዳዎች (1. የተመራቂዎች ሥራ-አጥነት 2. የኑሮ ውድነት ሸክም 3. የአነስተኛና ጥቃቅን ችግር
 • በወንጀል ጉዳይ በስህተት የተሰጠ የመጨረሻ ፍርድ በሚል ርዕስ በሕግ ጉዳይ ቃለመጠይቅ ከአቶ አሰፋ ከሲቶ ጋር
 • የገሐነሙ ጉዞ ‹‹የእኛ ሰዎች በየመን›› አልአዛር ኬ
 • ጨጓራ እና ‹ሙሉ በግ…› ኤፍሬም እንዳለ በ እንጨዋወት
 • የሸገር ሬዲዮ መዓዛ
 • የጋምቤላ ሬዲዮ በቴክኒሺያን እጦት ተቋረጠ
 • ኢቢኤስ ተመልካች በትዕግስት እንዲጠብቀው ጠየቀ 
 • የኢህአዴግ ልሳን ‹‹አዲስ ራዕይ›› በመቶ ብር ሊሸጥ ነው (ገቢው ለጠ/ሚ መለስ ቤተመዘክር ግንባታ ይውላል
አድማስ በተለመደው የርዕሰ አንቀጽ ዘዬው  ‹‹እወርካ ሥር የገደለ፣ ዘወትር እወርካ ሥራ ያደፍጣል!›› የሚል ርእሰ አንቀጽ ይዞ ወጥቷል፡፡
ሰንደቅ ጋዜጣ  (ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005)
በዋናነት በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት እና በሙስና ችግሮች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደውንና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት በቦታው ተገኝቶ በመዘገብ የሰራውን ፕሮግራም በማያውቀው ሁኔታ ተለውጦ እና ተቆራርጦ ለሕዝብ እንዲቀርብ ተደርጓል ሲል የድርጅቱ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ አስታወቀ  ብሏል ሰንደቅ በፌት ገጽ ዜናው።
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ በዕለቱ ዝግጅቱን እንዲከታተል ተመድቦ ዜናው ከስድስት ደቂቃ ተኩል በላይ ሠርቶ በዕለቱ መተላለፉን፣ የዜናው ይዘትም አዎንታዊ ግብረ-መልስ ከውይይት ተሳታፊዎች እንደነበረው አስታውሷል። ይኸው የባለሥልጣናት ውይይት ሰፋ ባለ ፕሮግራም እንዲዘጋጅም ከድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች መታዘዙንና ይህንንም ተከትሎ በማግስቱ ቅዳሜ ዕለት ሰፊ ፕሮግራም አዘጋጅቶ እሁድ እንደሚተላለፍ የሚገልፀውን ማስታወቂያ (ስፖት) ሠርቶ አስረክቦ በግል ጉዳይ እረፍት መውሰዱን አስታውሷል።
ሆኖም እሁድ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ይተላለፋል የተባለው ፕሮግራም እሱ ለጊዜው ባላወቀው ምክንያት ሳይተላለፍ መቅረቱን፣ ነገር ግን ስብሰባውን በአካል ተገኝቶ ያልተከታተለው አቶ ሳሙኤል ከበደ የተባለ ባልደረባው አማካይነት ቀደም ሲል አዘጋጅቶት የሄደው የተሟላ ፕሮግራም ተጥሎ፣ ሆን ተብሎ የባለሥልጣናቱ ኀሳቦች ተቆራርጦ ማክሰኞ ጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲተላለፍ መደረጉን ገልጿል።

ጋዜጠኛ አዲሱ አያይዞም ይህን መሰል ችግር የሚፈጠረው በቢሮክራሲ ውስጥ ከኢሕአዴግ በላይ ኢሕአዴግ ነን የሚሉ ሰዎች በመኖራቸው ነው። በስብሰባው ውስጥ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል ፕሮግራሙ እሁድ ባለመተላለፉ ቅሬታቸውን ለድርጅቱ ኃላፊዎች ማቅረባቸውንም ሰምቻለሁ ብሏል። የተቋሙን ኃላፊዎች ለማነጋገር ከፍተኛ ጥረት ብናደርግም አልተሳካልንም ብሏል ሰንደቅ በዜናው፡፡

አጫጭር ወሬዎች  ሰንደቅ
 • አምባሳደር ተወልደ ገብሩ ከትግራይ ልማት ማኅበር ኃላፊነታቸው ለቀቁ
 • አልኮልና አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅመው መኪና የሚያሽከረክሩትን የሚለይ ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ ሊውል ነው
 • ነጋዴዎች በካሽ ሬጅስተር አሰራር መቸገራቸውን ገለፁ
 • ኢትዮጵያ የሰራተኛ የመደራጀት መብት  ከማያከብሩ አገሮች አንዷ ተባለች ILO ይሄን ይላል UN ደግሞ የሰብአዊ መብት አባል ያደርጋል፡፡
 •   ኤስ ቴሌቪዥን ታፍኜአለሁ አለ
 • ግምቱ አምስት ሚሊዮን ብር የሆነ አምስት ሔክታር ደን ሊጨፈጨፍ ነው
 • ማይክሮ ሶፍት ህገ-ወጥ ስርጭትን በኢትዮጵያ ለመቆጣጠር ስምምነት ተፈራረመ
 • በኢትዮጵያ የሚገኘው የሶማሊያ ስደተኞች ካምፕ የአለማችን ሁለተኛው ትልቅ ካምፕ ሆነ

አዲስ ጉዳይ (የ6ኛ ዓመት ልዩ ዕትም)
አዲስ ጉዳይ መጽሄት አድስ ጉዳይ የሆነችበትን 6 ተኛ አመት በልዩ እትም አክብራለች ፡፡ በዚህ ልዩ እትም በትውልድ ዙሪያ ሰፌ ጽሁፎችን ይዛ የወጣች ሲሆን ያ ትውልድን በተመለከተ
 • የ ‹ያ ትውልድ› ተጠየቅ!
 • ያ ትውልድ ይመለስ ይሆን
 • ‹‹ኑሮ›› በዚያና በዚህ ትውልድ ሕይወት
የሚሉ ጽሁፍችን አስነብባናለች፡፡ጠንካራ ቃለ መጠይቅ በሚያስነብበን የቃለ መጠይቅ አምድም ‹‹ይሄ ትውልድ በቂምና በቀል የተበከለ አይደለም›› ሲሉ  አለማየሁ ረዳ (ዶ/ር) በትውልዶች ዙሪያ ከአዲስ ጉዳይ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ቋሚ አምደኞች  ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ ‹‹መጋኛ እና ምች›› ፣ ዳንኤል ክብረት ዶሮና የሁለት ልጆች ፈተና  ፣አንጋፋውና ወጣቱ ትውልድ በመስፍን ሀብተማርያም፣በሌለ በሬ ማረስ በጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ከአብዮት ፍንዳታ እስከ ዘመነ ‹‹ፍንዳታ›› ኤፍሬም እሸቴ የሚሉ ጽሁፎችን አስነብበዋል፡፡ በኃይሉ ገ/እግዚአብሔርም ያኔ ና ዘንድሮ ብሎ ከትውልድና ከድሮ ጋር የተያያዘ ጽሁፉን አስነብቧል፡፡
የቤት ልማቱና ኢንቁፍቱ የሚለው ጽሁፍም በውስጡ ‹‹በኢትዮጵያ ውስት የምርጫ ወቅትን አስታከው ግርር…የሚሉ በርካታ ‹‹ኢንቁፍቱ ዝንቦች›. የቤት ልማቱን ሥራ ተገን አድርገው ሲሯሯጡ በሶስቱም ሥረዓቶች ታይተዋል››  ይለናል፡፡ በተከታታይ እትሞቹ ቀዝቃዛ ሆኗል ተብሎ ሲታማ የነበረው አዲስ ጉዳይ ወደ ቀድሞው አቋሙ የተመለሰ ይመስላል፡፡
ርዕሰ አንቀጽ ልደት የስድስት ዓመታት የአዲስ ጉዳይ መንገድን ይዘረዝራል እንዲሁም በሌላ ርዕሰ አንቀጽ ‹‹ምንም ያልኖረው ያ ትውልድና ምንም የሌለው ይሄ ትውልድ ብሎ የትውልድ እትሙን በርእሰ አንቀጽም ለአዲሱ ትውልድ እድል መስጠት እንደሚገባ ገልፅዋል፡፡ 
ወደ ፓለቲካ  እና ማህበራዊ መጽሄትነት ጠቅልሎ የገባው ቆንጆ መጽሄት  ጠሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ እምነት+ፖለቲካ =አስተሳሰብ የሚለውን ጽሁፉ ጠ/ሚኒስትሩን የፓለቲካ እና የእምነት መምታታት ለመተቸት ሞክሯል፡፡ በተያያዘ የፓለቲካ ጽሁፍ ኢህአዴግ መለሲዝም እየሆነ ይሆን? በሚለው ጽሁፍ ቆንጆ የአቶ መለስን ከሞት በኃላ ያለ ሚና ወደ መለሲዝም ተጠግቷል ብሏል፡፡ አረ የኔትወርክ ያለህ? የቴሌን የሰሞኑን የኔትወርክ መቆራረጥ የተቸበት ሲሆን የአላሙዲና የባለስልጣኖቻችንን ወዳጅነት በምን እንለካው? በሚለውጽሁፍ የባለሃብቱን እና የባለስልጣናትን ግንኙነት የሚያነሳሳ ጽሁፍ አስነብቧል፡፡
 በእምነት ተቋማት ጉዳዩች በተለይም ለኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ በቤተክርስቲያን የተለየ ትኩረት የሚሰጠው እንቁ መጽሄት   በዚህ ሳምንትም ‹‹ዜና ቤተክርስቲያን›› የሚል ጽሁፍ አስነብቦናል፡፡ ‹‹በህዳር ጢስ ማጤን ለምን?›› ታዲዮስ ግርማ፣‹‹ዛሬም የማለመደው ሰቆቃና ድምጽ አልባ ደላሎቻችን›› በነብዩ ሲራክ፣ እንዲሁም ስለ ግብጽ እና ሱዳን የደህንነት ስጋትን በተመለከተ 
‹‹ሱዳንና ግብጽ እኛን ለማጥቃት ኤርፖርት ከገነቡ ቀድመን መምታት አለብን›› ‹‹ግብጾች በኢትዮጵያ ምድር ወታደራዊ ጥቃት አይሞክሩም›› ሲሉ  ብርጋድየር  ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ ለእንቁ ተናግረዋል፡፡ በተለመደው የኢንተርኔት ጽሁፎችን የማተም ሰሞንኛ የህትመት ሚዲያዎች ልምድ መሰረት ኢትዮጵያ ከኦባማ ምርጫ ምን መጠበቅ ትችላለች›› የሚለውን የፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም ጽሁፍ እንቁ ለንባብ አውሎታል፡፡
ቅርቃር ውስጥ የገባው የዕርቀ ሰላም ድርድር  የሚለው ጽሁፍ ተጀምሮ ብዙም የመግፋት አዝማሚያ ስላላሳየው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እርቀ ሰላም ለመናገር ሞክሯል፡፡ 
ላይፍ መጽሄት በበኩሉ  የትራንስፖርት ትርምስ እስከመቼ የሚል ሰፋ ያለ ጽሁፍ ያስነበበ ሲሆን የአዲስ አባባ ከተማን የትራንስፓርት ችግር ጠንከር አድርጎ ተችቷል፡፡ የኤርትራውያን ሰቆቃ  በሲናይ በረሃ በሚል የኤርትራውያንን የስደት መከራ የሚያሳይ ጽሁፍ፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የኦሮሞን ሕዝብ ምን እያሉት ነው የሚል አቶ ብልቻን ንግግር ለመተቸት የሚሞክር ሌላ ጽሁፍ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ላይፍ ያስነበባቸው ጽሁፎች ነበሩ፡፡
ከአለማቀፋዊ ዜናዎች ጋር ተያይዞ ሶርያ- ከህዝባዊ አብዮት ማካሄጃ ወደ አሸባሪ ዓመጽ ማራመጃ ሲል ፊልም ሰሪ ታምሩ ብርሃኑ ባለስልጣን መሆን አልፈልግም ማለቱንም ነግሮናል፡፡

ቃልኪዳን መጽሄት የሚከተሉትን ዋና ዋና ሃሳቦች የያዙ ጽሁፍችን ይዞ ለገበያ ቀርቧል፡፡
 • ‹‹በኩዌት ከፎቅ የዘለሉት ኢትዮጵያውያን እህትማማቾች››
 • ‹‹እነ አቼኖ ቦታ ይልቀቁ! አሁን የጊዮርጊስ ቁጥር አንድ አስጨፋሪ እኔ ነኝ›› የጊዮርጊስ የግራ ትላ ፎቅ አስጨፋሪ ጮሬ
 • የፍሪላንሰሩን ኑሮ፣ ድሮና ዘንድሮ (ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ መታሰቢያ)
 • በሴቶች የተከፈተው ጦርነት ወዴት እያመራ ነው ከአሲድ…ስለት…ቦምብ…የጥይት እሩምታ ቀጥሎስ - ኒውክለር
 • ሐውልቱ ይፍረስ ግራዚያኒ ይደምሰስ አጥናፉ አለማየሁ
 • ሥራ ፍለጋና ውሎ በዓለምሰው መለሰ
ሪፖርተር (እሁድ ኅዳር 16 ቀን 2005 ዓ/ም)
 • በሽብርተኝነት የተከሰሱ 29 ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ ተጠየቀ::
 • የሱሉልታ ከተማ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣናት ጉቦ ሲቀበሉ ተያዙ::
 • ዘመን ባንክ ይግባኙን በማንሳት የተወሰነበትን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ተስማማ::
 • የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ግብይት ገቢ ቀንሷል::
 • ርዕሰ አንቀጽ  መርሆች ገጠመኞች እንዳይሆኑ እንጠንቀቅ ::
 • በአዲስ አበባ ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መካከለኛ ኩባንያ ሊሆኑ ነው::

ከAddis Standard የእንግሊዘኛው  መጽሄት  እነዚህ ሁለት ጽሁፎች ግን ሊነበቡ ይገባቸዋልና የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው ሙሉ ጽሁፎችን ያንብቡ፡፡
“PM Hailemariam offers lucrative incentives to animal husbandry and meat export businesses but he may wish to fix the country’s institutional mess first”  
Tsedale Lemma 
ምርቃት (ከአድማስ ከግጥም ጥግ)
አንዴ ብቻ
አንዴ መውደቅና አንዴ መነሳት፣
እኩል ይመስላሉ በቀላል ስሌት፣
ግን እኩል ኤደሉም ይበላለጣሉ፣
አንዴ ብቻ ወድቀው የቀሩ ብዙ አሉ፡፡
አንድነት ግርማ

ሰናይ ቀን ለሁላችን፡፡

No comments:

Post a Comment