Friday, July 17, 2015

“አልከላከልም “

ትርጉም፡ አቤል ዋበላ
አርትኦት፡ ናትናኤል ፈለቀ
ከዳኞቹ አንዱ እንደ ከሳሽ አቃቤ ሕግ የሚያገለግለው ክሱን አነበበ፡፡
‹‹አሁን ራስህን መከላከል የሚያስችልህን ማንኛውም ምክንያት ማቅረብ ትችላለህ፡›› ሲል አስታወቀ፡፡
አቶ ሃንክ ሪርደን ፊቱን ወደ መድረኩ አዙሮ በልዩ ሁኔታ ግልፅ በሆነ ባልተሸበረ ድምፅ መለሰ፡፡
‹‹ምንም መከላከያ የለኝም››
‹‹እራስህን…….›› ዳኛው እየተደነቃቀፈ ተናገረ፡፡ እንደዚህ ቀላል ይሆናል ብሎ አላሳበም ነበር፡፡ ‹‹ እራስህን ለፍርድ ቤቱ ምህረት አሳልፈህ ትሰጣለህ››
‹‹
ይህ ፍርድ ቤት ይዳኘኝ ዘንድ እውቅናን አልሰጥም›› 
‹‹
ምን?››
‹‹
ለዚህ ፍርድ ቤት ዳኝነት እውቅና አልሰጥም››
‹‹
ግን አቶ ሪርደን ላይ ይህ ፍርድ ቤት እንደዚህ ዓይነት ወንጀሎችን እንዲመለከት በሕግ የተሰየመ ነው››
‹‹
የእኔን ሥራ እንደወንጀል አይቆጥረውም››
‹‹
ግን ብረታ ብረት መሸጥን ለሚቆጣጠረው ስልጣናችሁ እውቅና አልሰጥም?››
‹‹
ያንተ እውቅና እንደማያስፈልግ መግለፅ አስመፈላጊ ይመስለኛል››
‹‹
የለም ይህንን በሚገባ እገነዘባለሁ፤ በዚህ መሠረት እየተወንኩኝ ነው››
የቤቱን ፀጥታ አስተዋለ፤ አንደኛው አንደኛውን ለጥቅም ሲል በሚጫወቱት ውስብስብ የማስመሰል ህግ የእርሱን አቋም ለመረዳት የሚያስቸግር ጅልነት አደርገው በወሰዱት ነበር፡፡ ግን ምንም አልነበረም፡፡ በእርጋታ ተቀምጠዋል፣ ተረድተውታል፡፡
‹‹
ለሕግ መታዘዝን አሻፈረኝ ማለትህ ነው?›› ዳኛው ጠየቀ 
‹‹
የለም ለህጉ እሺታዬን እየገለፅኩኝ ነውለተፃፈው፡፡ የእናንተ ህግ ሕይወቴን፣ ሥራዬንና ንብረቴን የያዘ ምን አልባትም ያለ ፈቃዴ የሚያስወግድ ነው፡፡ በጣም ደህና - አሁንም በነገሩ ላይ ተሳትፎ ሳይኖረኝ አስወግዱኝ፡፡ ምንም መከላከል በማይቻልበት ራሴን የመከላከልን ክፍል ወክዬ መጫወት አልፈልግም፡፡ እናም በፍትሕ አደባባይ የመዳኘት ብዥታን ማስመሰል አልፈልግም፡፡››
‹‹
ግን አቶ ሪርደን፣ ህጉ በዝርዝርና በማያሻማ መልኩ በአንተ በኩል ያለውን ክርክር እንድታቀርብና ራስህን እንድትከላከል ዕድል ይሰጥሃል››
‹‹
ወደ ችሎት የመጣ እስረኛ ራሱን መከላከል የሚችለው በዳኞቹ እውቅና ያለው ያልተዛባ የፍትህ መርህ ሲኖር ነው፡፡ መብቱን የሚያስጠብቅ፣ እነርሱ (ዳኞቹ) የማይጥሱት እርሱ ደግሞ የሚሸሸግበት መርኅ ! እናንተ እኔን እየዳኛችሁበት ያለው ሕግ ምንም የያዘው መርህ የለም እኔም ምንም መብት የለኝም፤ በእኔ ላይ የወደዳችሁት ማድረግ ትችላላችሁ በጣም ጥሩ አድርጉት››
‹‹
ሙሉ በሙሉ
‹‹
ይህ ፍርድ ቤት በክሱ የቀረበው ጭብጥ ጥብቅ እንደሆነ ግንዛቤ ወስዷል ፡፡ ፍርድ ቤቱ ሊወስንብህ የሚችላውን ቅጣት 
እጅግ ከባድ ነው፡፡››
‹‹
ፈቅጃለሁ››
‹‹
ይቅርታህን እለምናለሁ?››
‹‹
ጫኑብኝ››
ሶስቱም ዳኞች እርስ በርስ ተያዩ አፈ ጉባኤው ወደ ሪርደን ዞሮ ‹‹ይሄ ተደርጎ አይታወቅም›› ሲል ተናገረ፡፡
‹‹
ይሄ በጠቅላላው ስርአቱን ያልተከተለ ነው›› ሁለተኛው ዳኛ ተናገረ፡፡ ህጉ ለራስህ መከላከያ የሚሆን ክርክርህን እንድታቀርብ ያዛል፤ አሊያም ያለህ ብቸኛ አማራጭ ራስህን ለፍርድ ቤቱ ምህረት አሳልፈህ እንደሰጠህ ማስመዝገብ ነው››
‹‹
አላደርገውም››
‹‹
ግን ማድረግ አለብህ››
‹‹
ካንተ አንዳች የፍቃደኝነት ድርጊትን እየጠበቅን ነው ማለታችሁ ነው?››
‹‹
አዎን››
‹‹
በፍቃደኝነት ምንም አላደርግም››
‹‹ህጉ በተከሳሽ በኩል ያለው ክርክር እዲመዘገብ ያስገድዳል››
‹‹
ይህንን ሂደት ህጋዊ ለማድረግ ያንተን እርዳታ እንፈልጋለን ማለታችሁ ነው?››
‹‹
እኛ እንደገባን›› ዳኛው ጠየቀ፡፡ ‹‹የራስህን ፍላጎት ከማኅረሰቡ ፍላጎት በላይ አድርገህ አስቀምጠሃል?››
‹‹
እንደዚህ አይነት ጥያቄ በበላዔ-ሰብ (ካኒባል) ማኅበረሰብ ካሆነ በቀር መቼም ሊነሳ አይችልም››
‹‹
ምን ……ምን ማለት ነው?››
‹‹
ያልተገባን ክፍያ በማይጠይቁና የሰው ልጅን መስዋእት የማድረግ ልማድ በሌላቸው ሰዎች መካከል የፍላጎት መቃረን ይኖራል ብዬ አላስብም››
‹‹
እኛ እንደገባን ማኅበረሰቡን ትርፍን መገደብ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ያን የማድረግ መብት እንዳለው ትረዳለህ?››
‹‹
ለምን? አዎን እረዳለሁ ማኅበረሰቡ የኔን ትርፍ መጠን መገደብ ከፈለገ የኔን ምርቶች በለመግዛት ያን ማድረግ ይቻላል››
‹‹
እና እየተናገርን ያለው….ስለሌሎች መንገዶች ነው››
‹‹
ከዚህ ሌላ ማንኛውም የትርፍን መጠን መገደቢያ መንገድ የዘራፊዎች ነው በሚል እገነዘበዋለሁ››
‹‹
አቶ ሪርደንይህ አካሄድ ራስህን የመከላከል መብትህን ያጣበዋል››
‹‹
ራሴን እንደማልከላከል ተናግሬያለሁ››
‹‹
እንደዚህ ያለ ተሰምቶም አይታወቅ! የቀረበብህን ክስ ክብደት አስተውለኸዋል?››
‹‹
ስለእርሱ ማሰብ ግድ አይሰጠኝም››
‹‹
ይህ አቋምህ የሚያስከትለውን ውጤት ተገንዝበኸዋል?››
‹‹
የለም …..አዎን…. ምን ያን የምናደርገው ስርዓቱን ለማሟላት ነው››
‹‹
እኔ አልረዳችሁም››
በሶስቱ ዳኞች መካከል እንደ ከሳሽ ያገለገለው እና በእድሜ የሚያንሰው ዳኛ በቁጣ ተናገረ ‹‹ይህ ከምር ሊወሰድ የማይችል እና ተገቢ ያልሆነ ነገር ነው እንዳንተ ያለ ብዙ ማድረግ የሚችል ሰው ከባድ ቅታት ሊጣልብህ ሲል ምንም ….››
በራሱ ሰዓት ንግሩን ቀጨው፤ በፍርድ ቤቱ የኋላ ወንበር የተቀመጠ ሰው በረዥሙ አፏጨ፡፡
‹‹
እኔ እምፈልገው›› ሪርደን ጥልቅና ሻካራ በሆነ ድምጽ ተናገረ፡፤ ‹‹ይህ ስርዓት ምን ዓይነት እንደሆነ ማሳየት ነው፡፡ ይህንን ለመደበቅ የእኔን እርዳታ ከፈለጋችሁ አልረዳችሁም››
‹‹
እኛ ግን ራስህን እንድትከላከል እድል እየሰጠንህ ነው….አንተ ነህ ሳትቀበል የቀረኸው››
‹‹
እድል እንዳለኝ አያስመሰልቡኝ አልረዳችሁም፡፡ መብቶች እውቅናን በሌላቸው ቦታ የእውነተኛ ገፅታ ጠብቆ ለማቆየት አልተባበራችሁም፤ የጠመንጃ አፈሙዝ የክርክ መቋጫ በመሆነበት ወደበላ ልበልሃበመግባት የምክንያታዊነት ገፅታን ጠብቆ በማቆየት አልተባበራችሁም፡፡ እናንተ ፍትህን በትክክልና በህጉ መሰረት የምትሰሩ በማስመሰል አልረዳችሁም፡፡››
‹‹
ህጉ ግን በፈቃደኝነት እንድትከላከል ያስገድድሃል››
በፍረድ ቤቱ ከወደ ጀርባ ሳቅ ይሰማ ነበር፡፡
‹‹
የተከበራችሁ የእናንተ ንድፈ-ሃሳብ ጉድለት ነው›› ሪድረን በጥልቀጥና በሻካራ ድምፅ ተናገረ፡፡ ‹‹ እኔም ከዚህ ተነስቼ አልረዳችሁም፡፡ ሰውን በማስገደድ መነጋገር ከፈለጋችሁ አድርጉት፡፡ ያን ለማድር ግን የእናንተ ጥቃት ሰለባ የሆነው ሰው የፍቃደኝነት ትብብር እንደሚያስፈልገው አሁን ከምታዩት በብዙ መንገዶች በበለጠ ኋላ ትደርሱበታላችሁ፡፡ የእናንተ ተጠያቂዎች ደግሞ እናንተን የሚያስችላችሁ (እናንተ ለመተግበር የማይቻችሁ) የእነርሱ ፈቃድ መሆኑን ይደርሱበታል፡፡ በፅኑነት መቆየትን እመርጥና በምትጠይቁት ሁኔታ ሁሉ እታዘዛችኋለሁ፡፡ ለጠመንጃ አፈሙዝ የፈለጋችሁትን ምንም ነገር አደርጋለሁ ወደ ወህኒ እንድወርድ ከፈለጋችሁእኔን ተሸክመው እንዲወስዱኝ የታጠቁ ሰዎች መላክ አለባችሁ፡፡ በፍቃዴ አልንቀሳቀስም፡፡ በገንዘብ ከቀጣችሁኝ ቅጣቱን ለመረከብ ንብረቴን መያዝ አለባችሁ በፈቃዴ ግን አልከፍልም፡፡ እኔን በሃይል በማስገድ መብት እንዳላችሁ ካመናችሁ ጠመንጃችሁን በግልፅ ተጠቀሙ፡፡ ድርጊታችሁን በመደበቅ አልረዳችሁም፡፡››
ሽማግሌው ዳኛ በጠረጴዛው ላይ ወደፊት ጠቃ ብሎ ኩራት ባለው የፌዝ በሚመስል ድምፅ ተናገረ፡፡ ‹‹ አቶ ሪርደን እንየተናገርክ ያለኸው ለሆነ መርህ የምንታገል በማስመሰል ነው፡፡ ነገር ግን እየታገልክ ያለኸው ስለ የግል ንብረትህ ብቻ ይመስለኛል፡፡ አይደለም እንዴ?››
‹‹
አዎን እየታገልኩኝ ያለሁት ስለ የግል ንብረቴ ነው፡፡ ይህን ይህነ የሚወደስ የመርሕ ዓይነት ታውቃላችሁ?››
‹‹
አቋቋምህ አንደ ነጻነት ታጋይ ነው ነገር ግን የቆምከው ገንዘብ ስለማግኘት ነፃነት ብቻ ነው››
‹‹
አዎን እርግጥ ነው በአጠቃላይ የምፈልገው ገንዘብ የማግኘት ነፃነት ነው፡፡ ነፃነት ምንን እንደሚያመላክት ታውቁታላችሁ?››
‹‹አቆ ሪርደን በእርግጠኝነት አኳኋንህን አሳስተን እንድንረዳው አትፈልግም ፡፡ ከትርፉ በቀር ሌላ ነገር የማይሰራ፣ ለወጣበት ማኅበረሰብ ደህንነት ምንም የማይገደው፣ ማህበረሰባዊ ግንዛቤ የጎደለው በሚል ለተሰራጨው ግምት ማጠናከሪያ መስጠት አትፈልግም፡፡››
‹‹
ለራሴ ትርፍ እጂ ሌላ ምንም ነገር አልሰራም ያን ደግሞ አግኝቼዋለሁ››
ከጀርባው ከተሰበሰበው ህዝብ የማጉረምረም ድምፅ ተሰማ ፡፡ የቁጣ ግን አልነበረም የአድናቆት እንጂ፡፡ ዳኞቹ ዝም እንዳሉ ናቸው፡፡ በእርጋታ መናገሩን ቀጠለ፡፡
የለም ሁኔታዬን በተሳሳተ መልኩ እንድትረዱኝ አልፈልግም፡፡ ይህ እንዲመዘገብልኝ ሳደርግ ደስታ ይሰማኛል፡፡ ስለ እኔ በጋዜጦች ስለተነገረው እውነታ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ በግምገማቸው ግን አይደለም፡፡ የምሰራው ለራሴ ትርፍ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ ያንን የማደርገው ሰዎች የሚፈልጉትንና ለመግዛት የሚችሉትን ምርት ለመሸጥ ነው፡፡ ለእነርሱ ጥቅም ስል እኔ ተጎድቼ አላመርትም፡፡ እነርሱም ለእኔ ጥቅም ሲሉ ተጎድተው አይገዙኝም፡፡ ለእነርሱ ስል ፍላጎቴን መስዋዕት ማድረግ አልፈልግም፡፡ እርሱም ለእኔ ሲሉ የእነርሱም መስዋዕት አያደርጉም፡፡ የምንደራደረው በጋራ ፈቃድ ለጋራ ጥቅም በእኩልነት ነው፡፡ በዚህ መንገድ የማገኘው እያንዳንዷ ሽርፍራፊ ሳንቲም እኮራለሁ፤ ሃብታም በመሆኔ የራሴ በሆነው በእያንዳንዱ ሳንቲም የምኮራ ሰው ነኝ፡፡ ገንዘቤን ያገኘሁት በራሴ ጥረት ነው፤ በነጻ ልውውጥና በፈቃደኝነት ከተደራደርኩበት እያንዳንዱ ሰው፣ ሲጀመር በፈቃደኝነት ባሰሩኝ ሰዎች አሁን ደግሞ ለእኔ በፈቃደኝነት ተቀጥረው በሚሰሩልኝ ሰዎች ምርቶቼን በፈቃደኝነት በሚገዙኝ ሰዎች ነው፡፡ 
በግልፅ እኔን ለመጠየቅ ለፈራችሁ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ልስጥ ፡፡
ለሰራተኞቼ የሰጡኝን አገልግሎት ከሚያወጣው በላይ መክፈል እፈልጋለሁ? አልፈልግም፡፡ 
ደንበኞቼ ምርቶቼን ሊገዙ ፍቃደኛ ከሆኑት ዋጋ በታች እንዲከፍሉኝ እፈልጋለሁ? አልፈልግም፡፡ 
በኪሳራ ወይም በነፃ መሸጥ እፈልጋለሁ? አልፈልግም፡፡ ይህ ኃጢአት ከሆነ በያዛችሁት መለኪያ መሰረት ደስ የሚያሰኛችሁን ምንም ነገር አደርጉብኝ፣ እነዚህ የእኔ መለኪያዎች ናቸው ፡፡ መተዳደሪያን እያገኘሁ ያለሁት ማንኛውም ሃቀኛ ሰው እንደሚያደርገው ነው፡፡ በሕይወት መኖሬንና ኑሮዬን ለማሸነፍ የመስራቴን እውነት ወንጀል የሚያደርግን ለመቀበል እምቢ እላለሁ፡፡ መስራቴን እና በጥሩ ሁኔታ የመስራቴን እውነት ወንጀል የሚያደርግን ለመቀበል እምቢ እላለሁ፡፡ ከአብዛናው ሰው የተሻለ ሁኔታ መስራት የመቻሌን እውነት፣ ስራዬ ከጎረቤቶቼ ስራ የበለጠ ዋጋ እንዳውና ብዙ ሰዎች ሊከፍሉኝ ፍቃደኛ የመሆናቸውን እውነት ወንጀል የሚያደርግን ለመቀበል እምቢ እላለሁ፡፡ ስለችሎታዬ ይቅርታ መጠየቅን እምቢ እላለሁ፡፡ ስለስኬቴ ይቅርታ መጠየቅን እምቢ እላለሁ፡፡ ስለግንዛቤ ይቅርታ መጠየቅን እምቢ እላለሁ፡፡ ይህ ሃጢአት ከሆነ የምትችሉትን ሁሉ አደርጉ ፡፡ ይሄን ማኅበረሰቡ ለፍላጎቱ ጎጂ ሆኖ ካገኘው ማኅበረሰቡ እንዲያጠፋኝ ፍቀዱለት፡፡ እየተገዳደርኩት ያለሁት የእናንተን አንድ የተወሰነ ፖሊሲ ሳይሆን የሞራል መመሪያችሁን ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎችን መስዋዕት በማድረግ የተወሰኑ ሰዎችን ጥቅም ለማሳካት መቻሉ እውነት ቢሆን ኖሮ፣ ብጠየቅ በደሜ ጠብታ ዋጋነት መኖር የሚችሉ ሰዎች ካሉ ራሴን መስዋዕት አደርግ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ከጠቀስኩት በቀር ራሴን ጎድቼ የማኅበረሰቡን ፍላጎት እንዳገለግል ብጠየቅአሻፈረኝ እላለሁ፡፡ በጣም እንደለመድኩት ሰይጣን እዘነጋዋለሁ፡፡ ባኝ ሃይል ሁሉ እታገለዋለሁ ከመገደሌ በፊት አንድ ደቂቃ ቢኖረኝ እንኳን የሰው ዘርን ሁሉ እታገላለሁ፡፡ ውጊያው ፍትሃዊ እና ህይወት ያለውሰው ለመኖር ያለው መብት ስለሆነ በልበ ሙሉነት እታገላዋለሁ፡፡ ስለእኔ ምንም የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳይኖር፤ አሁን ራሳቸውን ማኅበረሰብ ብለው የሚጠሩት የኔ ከሳሾች እምነት ውቃቢያቸው ተጠቂ ከፈለገ እንዲህ ላለውየማኅበረሰቡ ጥቅም ገደል ይግባ፡፡ እኔ የዚህ አካል አይደለሁም፡፡››
የተሰበሰበው ሰው ጭብጨባ ተቀበለው፡፡


Ayn Rand, Atlas Shrugged
(page 441-445)

No comments:

Post a Comment